ዜና ብሥራት ዘሥላሴ! ሐኬተኛው እና መናፍቁ ዘላለም ረድኤት ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲወገድ ቋሚ ሲኖዶስ ወሰነ!
- መ/ር ፍሥሐ ጽዮን ደመወዝ በማስተማር ሥራ ብቻ ይወሰናሉ
- የአቡነ ጢሞቴዎስ ቀጣይነት እየተጤነ ነው
- የቅ/ሲኖዶሱ አስቸኳይ ስብሰባ ነገ እንደሚካሄድ ይጠበቃል
ጥቅመኛው፣ ሐኬተኛው (ክፋተኛው) እና መናፍቁ ዘላለም ረድኤት በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከያዘው የቀን መደበኛ መርሐ ግብር አስተባባሪነት እንዲወገድ ቋሚ ሲኖዶስ ከስምምነት ላይ ደረሰ፡፡
ቋሚ ሲኖዶሱ ከዚህ ዐቢይ የስምምነት ውሳኔ ላይ የደረሰው በኮሌጁ አስተዳደርና በደቀ መዛሙርቱ መካከል ላለፉት ስድስት ወራት እየተባባሰ የመጣውን ውዝግብ ለማጣራት የተቋቋመው ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርት መሠረት በማድረግ ከኮሌጁ መምህራንና የደቀ መዛሙርቱ መማክርት አመራሮች ጋራ ከመከረ በኋላ ነው፡፡
ትላንት እና ዛሬ ቋሚ ሲኖዶሱ በወቅታዊ የኮሌጁ ኹኔታ ላይ ሲያካሂድ በዋላቸው ተከታታይ ስብሰባዎች፣ አጣሪ ኮሚቴው የኮሌጁን አካዳሚያዊ እና አስተዳደራዊ ይዞታ ለማሻሻል ከአጭር እና ረጅም ጊዜ አኳያ በመፍትሔነት ያቀረባቸውን የውሳኔ ሐሳቦች መርምሯል፡፡ በዚህም መሠረት በኮሌጁ መደበኛ ደቀ መዛሙርት ቅሬታ ከቀረበባቸው መካከል አንዱ የኾነውና ተደራራቢ ሓላፊነቶችን የያዘው ዘላለም ረድኤት ከሐላፊነቱ መነሣት እንዳለበት ተስማምቷል፡፡
በአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት ላይ እንደተገለጸው፣ ዘላለም ረድኤት ‹‹መምህር፣ የቀን መርሐ ግብር ሓላፊ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽንና የአስተዳደር ጉባኤ አባል›› ነበር፡፡ በሐኬተኛውና መናፍቁ ዘላለም ረድኤት ላይ የታዩበትን ጉድለቶችና ድክመቶች ኮሚቴው በሪፖርቱ ገጽ 14 ላይ እንደሚከተለው ዘርዝሮታል፡-
- ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ በማስተርስ መርሐ ግብር ሞያቸው ያልኾነውን ትምህርት ማስተማር፡፡ በኮሌጁ ከመጀመሪያ ጀምሮ ለዲግሪ መርሐ ግብር የምርምር ዘዴ /Research Method/ የሚያስተምሩት በሞያው ልምድና ዕውቀት ያላቸው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሚመጡ መምህራን ናቸው፡፡ ለማስተርስ ፕሮግራም ደግሞ የበለጠ ስፔሻላይዝድ ያደረገ መምህር መኾን ይኖርበታል፡፡ በኮሌጁ የተደረገው ግን÷ በሞያው ልምድና ዕውቀት ያላቸው መምህር ተነሥተው መ/ር ዘላለም ያጠኑት ነገረ መለኰት ኾኖ ሳለ ምርምር ዘዴን ለማስተርስ ፕሮግራም ያስተምራሉ፡፡
- የቀን መርሐ ግብር አስተባባሪ ኾነው ሳለ ተማሪውንና መምህሩን አስተባብሮ አለመምራት፤
- መደበኛ ደቀ መዛሙርት በኩል ግን ‹‹ለሚያስተምሩት ትምህርት ብቁ አይደሉም›› ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡፡ እርሳቸው በኮሚቴው ፊት ከተማሪዎች ለሚቀርቡባቸው ቅሬታዎች እንዲከራከሩ ቢጠየቁም ኮሚቴውን ረግጠው ወጥተዋል፡፡ በዚህም ‹‹ብቁ መምህር አይደሉም›› የሚለውን ቅሬታ የተቀበሉት አስመስሏል፡፡
- ለአጣሪ ኮሚቴው ሥራ ተባባሪ ተባባሪ አለመኾን፡፡ ኮሚቴው ለሚያቀርብላቸው ጥያቄዎች ቀና ምላሽ አለመስጠትና እንዲስተካከሉ በኮሚቴው ለተሰጣቸው ሥራዎች ተባባሪ ኾኖ ከመገኘት ይልቅ ሥራዎቹ እንዳይሠሩ መሞገት፤