የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ ርዕዮት ዓለሙ በጸጥታ ኃይሎች ታሰረች
(DW) — የፍትህ ጋዜጣ አምደኛ ርዕዮት ዓለሙ በጸጥታ ኃይሎች ታሰረች። ዓርብ ዓርብ የሚወጣው ሳምንታዊ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ አቶ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ለዶይቸ ቬለ እንዳረጋገጡት፡ ትናንት የመታሰር ዕጣ የገጠማት አምደኛ ወይዘሪት ርዕዩት ዛሬ ከቀትር በኋላ ፍርድ ቤት ቀርባ ነበር። የአውራ አምባ ታይምስ ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬም ያለፈው መታሰሩ ተዘግቧል።
የፍትህን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ግን አርያም ተክሌ አነጋግራቸዋለች። ያዳምጡ