የአውራምባ ታይምስ ም/ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ታሰረ

”ጉዳዩ ከጋዜጣዋ ጋርም ሆነ ከሙያው ጋር ተያያዥነት የለውም” የመንግሥት የፀጥታ ተቋማት

”ጋዜጠኛው ለእስር የተዳረገበትን ምክንያትና የሚገኝበትን ሁኔታ መንግሥት ያሳውቀንአውራምባ ታይምስ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሰኔ 14 ቀን 2003 ዓ.ም. June 21, 2011)፦ የአውራምባ ታይምስ ም/ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እሁድ ሰኔ 12 ቀን 2003 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት አካባቢ በርካታ ቁጥር ባላቸው የፀጥታ ኃይሎች ተይዞ ከመኖሪያ ቤቱ መታሰሩን አውራምባ ታይምስ ከቤተሰቦቹ ማረጋገጡን ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ።