የሊቢያ ጦርነት፡ ኔቶ እና የአባል ሀገራቱ ተሳትፎ

የሊቢያ መሪ ሙአመር ኧል ጋዳፊ ጦር ኃይላት ከዓማጽያኑ ጋ ውጊያ በቀጠሉበት እና የሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ኪዳን ኔቶም በጋዳፊ ኃይላት አንጻር ጥቃቱን ባጠናከረበት ባሁኑ ጊዜ በኔቶ ጽህፈት ቤት ውስጥ የኪዳኑ አባል ሀገራትን ተሳትፎ በተመለከተ ውይይቱ ቀጥሎዋል።