ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ በኦነግ አባልነት እየሰከሰሰ በኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚያደርሰውን ግፍ እንደቀጠለ ነው

የወያኔ አገዛዝ የቀድሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ፋካልቲ ዲን የነበሩትን አቶ አበራ ደገፉን ጨምሮ በአራት ኦሮሞ ተከሳሾች ላይ የጥፋተኛነት ብይን ማሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል።

በግለሰቦቹ ላይ የተደረገው ክስ “የጥላቻ መልክት በማሰራጨት፣ ወጣቶችን በመመልመል፤ ከህገ ወጡ የኦነግ ድረጅት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ተንቀሳቅሰዋል” የሚል እንደሆነም ታውቋል። ከጥፋተኛ ተብዬዎቹ ሌላው አቶ ቶሎሳ ወልዴ የተባሉና ለረዥም አመታት በጠበቃነት የሰሩ ግለሰብ ናቸው።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑትን አቶ አበራ ደገፉን የሚያውቁ ግለሰብ ለዝግጅት ክፍላችን ባስተላለፉት መልክት፤ ግለሰቡ በአቶ መረራ ጉዲና የሚመራው የኦሮሞ ህዝብ ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ አባል ነበሩ።

በአገሪቱ ውስጥ ዋና ህግ ሰባሪ የሆነውና የህግ ተቋማትን ለግፍ ማስፈጸሚያነት የሚጠቀመው የወያኔ አገዛዝ፤ በህጋዊ ፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የሚሳተፉ ወይም በማህበረሰቡ ውስጥ ባላቸው ከፍተኛ ደረጃ እና ተሰሚነት የሚጠላቸውን ኦሮሞዎች በኦነግ አባልነት እየከሰሰ ለእስር እና ለሞት ፍርድ እንደሚዳርግ ይታወቃል።