ምክር ቤቱ በቀኝ ክንፍ ሲያጠቃ ዋለ
ግርማ ሠይፉ ማሩ
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሦስተኛ ዓመት ሁለተኛው ዓመት አጋማሽ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ መለስ ዜናዊ በሞት መለየት መንስዔ ከገባበት የሀዘን ድባብ ተላቆ ከወትሮ በተሻለ መነቃቃት እየታየበት እንደሆነ ይታመናል። ይህ እውነት ቢሆንም አንዳንዶች ምንም አዲስ ነገር የለም ይላሉ (የአዲስ አድማስን “ፓርላማው ጥርስ አወጣ” ዘገባን ልብ ይሉዋል።) አዲስ ነገር መኖሩ ግን እየታየ ያለ አውነት ነው።