ስለኢሳት ለኢትዮጵያውያን የተላከ መልዕክት
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
ኢትዮጵያ ሀገራችን የለየላት የዜጎቿ እሥር ቤት ከሆነች በጥቂቱ 22 ዓመታት አለፉ። ከ22 ዓመታት በፊት የነበረው ሥርዓተ መንግሥቷ አሳሪና ገዳይ ቢሆንም እንደሥርዓትና የገዢዎቹም ማንነት እንደሀገራዊ ስብዕና ሥርዓተ መንግሥቱ በኢትዮጵያዊ ወገናዊነቱ የማይታማ፣ የመንግሥት አገልጋዮችም በሀገር ወዳድነታቸው ጥያቄ ውስጥ የማይገቡ ከደነዝነታቸውና ድንቁርናን መሠረት ካደረገው ዕብሪታቸው በስተቀር ሌላ ጠላት የሌላቸው ገልቱ ሥርዓትና ጨካኝ ኢትዮጵያውያን ባለሥልጣናት እንደነበሩን የምናስታውሰው ነው።