የጊዮርጊሱ ግርግር – መልካም አዲስ ዓመት!
ምድረ ቺካጎ (ግርማ ካሣ) [email protected] ነሐሴ 27 ቀን 2002 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ጊዮርጊስ አካባቢ ነው። ሰዎች በአንድ ቦታ ተከማችተዋል። ግርግር ነገር ይታያል። በመንገድ የሚያልፉ አንድ አባት በመኪና ውስጥ አብረዋቸው ያሉትን «ምንድን ነው የተፈጠረው?» ይሉና ይጠይቃሉ። ሹፌራቸው መኪናውን ቀስ አድርጎ እንዲያቆም ያዛሉ። ከሹፌሩ ሌላ አብሯቸው መኪናው ውስጥ የሚገኝ አንድ ወጣት ከመኪናው ወርዶ፣ ነገሩ ምን እንደሆነ አጣርቶ እንዲመጣ ይልካሉ። ወጣቱ፣ ፈጥኖ ብዙ ሰዎች ወደ ተሰበሰቡበት ያመራል። እየሆነ የየነበረውን ተመልክቶ ይመለሳል።