የሠርግ ድግስ ቅንጦትና ድህነት

ለፍቅረኛሞች፤ ብሎም ለቤተሰብና ዘመድ- አዝማድ፤ በሠርግ ድግስ ፤ተመርቆ ጎጆን ቀይሶ፤ በሶስት ጉልቻ መተሳሰርን የመሰለ ታላቅ ደስታ፤ ያለ አይመስለንም። ግን የሠርግ ድግስ ባህላችን በተለይ ወደ ከተማዉ አካባቢ መልኩን የቀየረ ይመስላል።