የዓለም ዳያስፐራ – በዋሽንግተን ዲሲ – ለወጣቶች

በዓለም ዙሪያ ከሃገሮቻቸው ውጭ የሚኖሩ ሰዎች ዕምቅ አቅም ለየወጡባቸው ሃገሮችና ማኅበረሰቦች ጥቅም ሊውል የሚችልባቸውን ሁኔታዎች ለማበረታታት የታሰበው የዓለም ዳያስፐራ መድረክ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ግንቦት 5 እና 6 / 2005 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ ላይ በበርካታ የግል የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ የሚሠሩ ስመ ገናና ኢትዮጵያዊንና ኤርትራዊያን የተሣተፉ ሲሆን ከዓለም ዙሪያ የዳያስፐራው አባላት የሆኑ ከአንድ መቶ በላይ ሃገሮች የተገኙበት ነው፡፡

የዛሬ ሦስት ዓመት ተጠንስሶ ለሦስተኛ ጊዜ እየተካሄደ ያለው ዓለምአቀፍ የዳያስፐራ መድረክ “የሃሣብና የተግባር መገናኛ ሥፍራ” የሚል መርኅ ያለው ነው፡፡

የትውልድ ሃገሩን እየጣለ ወደ ሌሎች ሃገሮች የሚፈልሰው ሰው ቁጥር ባለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ በሦስት እጥፍ የጨመረ ሲሆን ዛሬ በዓለም ዙሪያ ከ215 ሚሊየን …