በየፊናችን እየተማረርን መማራችን ለበጎ ነው
ይነጋል በላቸው
እቲ ናይ ቀደም ሰላም ዘመን ክምለስ፤
ሰላም ኢልና ንዝመር ብሃደ መንፈስ። ...
(ከኤርትራው ተወላጅ ድምጻዊ ርዕሶም ገ/እግዚአብሔር የዘፈን ግጥም የተወሰደ)
ይሄ ኢሣት የሚባል ቴሌቪዥን በትዝታ ባህር እያስዋኘ ጊዜየንም ዕንባየንም እያስጨረሰኝ ነው። በግማሽ ሜትር ርቀት እሱው ጋ - እቲቪው አጠገብ - ከተደቀንኩ የሚያስነሳኝ የለም። ቤቴ ሁሌ በአምባጓሮ እንደታመሰ ነው። ቤተሰብ የሚፈልገውና እኔ የምፈልገው ለየቅል በመሆኑ ትንሹ አምባገነን ሆኛለሁ። ለነገሩ አምባነንነት የሚጀምረው ከቤት ነውና ይቺ ተፅዕኖየ እየተሰማችኝ መጥታለች። ምን ላድርግ?