የአፍሪቃ አንድነት እና የጋዜጠኞቹ ትዉስታ

ሁሉም ሐገራት ከቀጥታ ቅኝ አገዛዝ እና ከነጭ ዘረኞች ጮቆና ነፃ ወጥተዋል። አፍሪቃዉያን የእዉነተኛ ነፃነት ባለቤቶች፥ የሠላም፥ የዲሞክራሲ፥ የእኩልነት፥ የፍትሕ ባለመብቶች፥ የሐብታቸዉ እኩል ተጠቃሚዎች የሚሆኑበት ዘመን ግን-ዛሬም በሐምሳኛ ዓመቱ ሩቅ መምሰሉ እንጂ ቁጭቱ ከአፄ ሐይለ ሥላሴ-እስከ ክዋሚ ንኩሩማሕ፥