ዋናው ጤና ነው

ረሃብን ለማስወገድ በሚደረገው ዓለምአቀፍ ጥረት ውስጥ የጥንዚዛ፣ የአባጨጓሬ፣ የንብ፣ የተርብና የጉንዳን ዘሮችን ለምግብነት መጠቀም እጅግ ጠቃሚ ሚና ሊጫወት እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት የምግብና የግብርና ድርጅት – ኤፍኤኦ አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ በዓለም ዙሪያ አሁን እነዚህን ነፍሣት የዕለት ምግባቸው አድርገው የሚኖሩ ከሁለት ቢሊየን በላይ ሰዎች መኖራቸውን አመልክቶ በገንቢና አልሚ ምግቦች የከበሩ፣ በቅባት፣ በበረትና ሌሎችም ማዕድናትና ንጥረነገሮች የበለፀጉ ናቸው ብሏል፡፡

የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥም ጠቃሚ ናቸውና በመላው ዓለም መለመድ ያለባቸው የምግብ ዓይነቶች መሆን አለባቸው ሲል ኤፍኤኦ ሃሣብ አቅርቧል፡፡

በሌላ ዜና ደግሞ በአስም ለሚንገላታ በዓለም ዙሪያ ከሦስት መቶ ሚሊየን በላይ ለሚሆን ሰው መጠነኛም ቢሆን እፎይታን ሊያስገኝ ይችላል …