በሆሳዕና "ማክበር" – በቀራንዮ "መስቀል"
ኤፍሬም እሸቴ
ታላቁ የክርስቲያኖች ጾም፣ ዐቢይ ጾም እነሆ የመጨረሻው “ሰሙነ ሕማማት”/ስቅለት ላይ ደረሰ። ለእምነቱ ተከታዮች የአጽዋማት ሁሉ በኩር እና ዋነኛ (ዐቢይ) እንደመሆኑ ከምንም በዓል በላይ በታላቅ መንፈሳዊ ስሜት የሚከበር ነው። የእምነቱ ተከታይ ላልሆነውም ወገን ቢሆን የሚኖረው ባህላዊ አንድምታ ከፍ ያለ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ታሪኩን በደረቅ ንባብ ለሚመለከተውም ቢሆን ከዕለት-ተዕለት ሕይወቱ ጋር ሊያስነጻጽረው የሚችለው ብዙ ቁም ነገር እንደሚያገኝበት ጥርጥር የለኝም።