በታዳጊ ወጣቶች ላይ የሚከሰቱ የተለያዩ ችግሮችን ለማስወገድ የታሰበ መድረክ ተዘጋጀ
በ17 ዓመቷ ራሷን ያጠፋችው ወጣት ቤተሰቦች ልምድ ያካፍላሉ!
“በእኔ ቤተሰብ የደረሰ ልብ የሚሰብር ሀዘን በሌሎች ወገኖቼ ላይ ደርሶ ማየት አልፈልግም” (የኤደን ወላጅ አባት)
‘ልጄን እንደ ንግስት ነበር ያሳደኳት፤ የዚህ ሀገር ልጅ ምኑም አይታወቅም” የኤደን እናት ወ/ሮ በለጡ
ደራሲ ሐምራዊት ተስፋ በውይይቱ ላይ ትናገራለች!
የአማንዳ ቶድ ወላጅ እናት በውይይቱ ተካፋይ ናቸው!
Ethiopia Zare (ሰኞ ግንቦት 5ቀን 2005 ዓ.ም. May 13, 2012)፦ ባለፈው መስከረም 24 ቀን 2012 ዓ.ም በቫንኩቨር ካናዳ ህይወቷን ያጣችው የ17 ዓመት ታዳጊ ወጣት ኤደን ዘውዱ ቤተሰቦች በራሳቸው ቤተሰብ የደረሰ ሀዘን በሌሎች ወገኖች ላይ እንዳይደርስ ለማንቃት ተግተው እንደሚሰሩ አስታወቁ። በኖርዝ አሜሪካ ልጆችን ለማሳደግ የሚያስችሉ ጥናቶችን ያካተተ መጽሐፍ የጻፉት ደራሲ ሐምራዊት ተስፋም ተጋባዥ መሆናቸው ታውቋል።