የኢትዮጵያ ሙስሊሞች፥ ቴሌቪዥንና ባሕርዳር ዩኒቨርስቲ

የእስረኞቹ ጠበቃ እንዳስታወቁት ክሱን የመሠረቱት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጅሐዳዊ ሐራከት በሚል ርዕስ ባሰራጨዉ ፊልም የደንበኞቻቸዉን ሥም በማጥፋቱ ነዉ።በተያያዘ ዜና የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች በበኩላቸዉ ሐይማኖታዊ ነፃነታችንን ገፎናል ያሉት የዩኒቨርስቲዉ አስተዳደር ዉሳኔዉን ካልቀየረ እንደሚከሱ አስታወቁ።