የአቢዬይ ሰላም አስከባሪ ተግባሩን ‘እየተወጣ አይደለም’ ሲሉ የደቡብ ሱዳን ባለሥልጣን ወቀሱ
የንጎክ-ዲንካ ጎሣ የበላይ መሪ የሆነት ኩዎል ዴንግ ኩዎል የተገደሉት ከትናንት በስተያ ቅዳሜ ከሱዳን ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተው እየተመለሱ ሳሉ ነበር፡፡
በአካባቢው በከብት አርቢነትና በተንቀሣቃሽነት የሚኖሩት የምስሪያ ጎሣ አባላት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባንዲራ ታጅቦ ይጓዝ በነበረ የሚስተር ኩዎል ዴንግ የልዑካን ቡድን ላይ ከፍተውታል በተባለው ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት ከራሣቸው ከጎሣው መሪ ሌላ የተባበሩት መንግሥታት የላም አስከባሪ ኃይል አባል የሆነ አንድ የኢትዮጵያ ወታደር ተገድሎ ሌሎች ሁለት ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች መቁሰላቸው ታውቋል፡፡ የጎሣው መሪ ኩዎል ዴንግ ተሣፍረውበት የነበረው መኪና አሽከርካሪም መገደሉ ተነግሯል፡፡
አድራጎቱን ኢትዮጵያ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ሕብረትና ዩናይትድ ስቴትስ አውግዘውታል፡፡
የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር …