ድሪምላይነር አውሮፕላን በረራ መጀመሩ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ3 ወራት ያህል ከመሬት እንዳይነሳ በመላው ዓለም ታግዶ የቆየውን ድሪም ላይነር አውሮፕላን በማስነሳት ተሳፋሪዎችን ጭኖ መደበኛ በረራ አካሄደ። ጃፓን ድሪምላይነር አውሮፕላን ላይ ሰው ከማሳፈሯ አስቀድሞ መንገደኞች ያልተጫኑበት ከ200 በላይ የበረራ ሙከራዎችን እንደምታደርግ ጠቅሳለች።