የርዕዮት ዓለሙ የጤና ሁኔታ

የታመመችውን ርዕዮትን የቃሊቲ ማረሚያ ቤት በቀጠሮዋ መሠረት ሐኪም ቤት እንደማይወስዳት አባትዋ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። በሌላ በኩል ጋዜጠኛ ውብሸት ታዮ ከቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ወደ ዝዋይ እንዲዛወር መደረጉ ቤተሰቦቹና ወዳጅ ዘመዶቹ እንዳይጎበኙት እንቅፋት መሆኑ ተሰምቷል ።