ማስታወቂያ፦ የድረ ገጽ አድራሻ ለውጥ

የሎስ አንጀለስ ቅድስት ሥላሴ ወገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን  ሰበካ ጉባኤ ይህንን ዌብሳይት (http://www.kidistselassie.org) የዕለት ከዕለት የሰበካ ጉባኤ እንቅቃሴ እንድንዘግብበት ጥያቄ ሰላቀረበልን  ከዛሬ ጀምሮ አብነት ትምህርት ቤታችንን  “ደበሎ”  በሚል ስያሜ፤ http://debelo.org በማለት የቀየርነው መሆኑን ተጠቃሚዎቻችን እንዲያውቁት ስንገልጽ ይህ አጋጣሚ ግን የአብነት ትምህርት ቤታችንንም በተደራጀና ስፋት ባለው ሁኔታ ለማቅርብ እንደሚመች በአክብሮት እናሳስባለን።

ከዚህም በተጨማሪ  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ፖርታል (የመረጃ መግቢያ)  www.Ethioorthodox.org  ስለጀመርን የአብነት ትምህርት ቤታችንንም  የአብነት ትምህርት ቤት በኢንተርኔት የሚለውን ሊንክ በመጫን በዚያ በኩል ያገኙታል።

እስከ አሁን ድረስ ስለነበረን አገልግሎት እግዚአብሔርን እያመሰገን ወደፊትም በስፋት አገልግሎቱን እንደምንቀጥል እንገልጻለን።  ለዚህም ዘዎትር በጸሎተዎ አንዳይርሱን አስተያየትም ካለዎት ይጻፉልን። ደበሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአብነት ት/ቤት http://debelo.org ማንኛውም አይነት የቴክኒክ ችግር ካጋጠመዎት በኢሜይል አድራሻችን ይጻፉልን።