የአፍሪቃ እና የአዉሮጳ ሕብረቶች ግንኙነት

የሁለቱ ማሕበራት መሪዎች ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ ከተነጋገሩ በሕዋላ እንዳስታወቁት ግጭትና ጦርነት በሚካሔድባቸዉ የአፍሪቃ ሐገራት ሠላም ለማስፈን እና ሠብአዊ ርዳታን ለማቅረብ በሚጠቅሙ መስኮች ሁሉ በጋራ እየሠሩ ነዉ።ወደፊቱም ትብብራቸዉን አጠናክረዉ የሚቀጥሉበትን ሥልት ቀይሰዋልም።