የኢሳት 3ኛ አመት ክብረ-በዓል የሙስሊሞች ብቻ ነው እንዴ?

ተክለሚካኤል አበበ (ቶሮንቶ – ካናዳ)

1-       ጽሁፍ ካላበሳጨ ወይ ካላስጨበጨበ አይመቸኝም። ላለፉት ጥቂት ሳምንታት የሚያበሳጭ ወይ የሚያስጨፍር ርእስ ስጠብቅ ሳልጽፍ ቆየሁ። የኢትዮጵያውያን፤ በተለይም የአማርኛ ተናጋሪዎች ከቤንሻንጉል መባረር በራሱ በቂ አናዳጅና አሳዛኝ ክስተት በመሆኑ፤ እንዲሁም ሌሎች ስለጻፉበት እሱ ላይ ብዙ አልደክምም። ስለዚህ ሌላ አናዳጅ ርእስ ናፈቅኩ። ባለፈው ሰኞ፤ ከአድካሚው ውሎዬ እረፍት ለመውሰድ ወደኢሳት ድረ-ገጽ አመራሁ። የደንቡን አድርሼ ከኢሳት ድረገጽ ወጥቼ ለመሄድ ጣቴን ጠቅ ለማድረቅ ስንቀለቀል፤ በአይኔ የቀኝ ጠርዝ፤ በኢሳት ድረገጽ የግራ ማእዘን ላይ፤ ስድስት ሰባት ወንዶች የተደረዱበት ምስል አየሁና ተመለስኩኝ። አንዳንዶቹ የተለመዱ ፊቶች ናቸው። “ሲሳይ አጌና፤ ታማኝ በየነ፤ ሻምበል በላይነህ፤ ሄኖክ የሺጥላ …” ከኢሳት ጋር በተያያዘ አንዳንዶቹ አዳዲስ ናቸው። የኢሳት ሶስተኛ አመት ዝግጅትን ለማድመቅ የተመረጡ እንግዶች ናቸው። የሚያበሳጭም ባይሆን፤ እነሆ የሚያወያይ ርእስ ተደግሶልኝ አየሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ …