በሁለት ወር ውስጥ ከ15 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ የመን ተሰደዋል
- የመን ውስጥ ምላሱ የተቆረጠውን ሀፊዝ ጨምሮ 25 ኢትዮጵያዊያን ሆስፒታል ገብተዋል
- ዮርዳኖስን መኪና ላይ አስረው መሬት ለመሬት ጎተቷት፣ (ሚሚ) ተደፈረች … ቃለምልልስ
ግሩም ተ/ሀይማኖት
የመን ውስጥ ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሰው በደል ከእለት ወደ እለት እየጨመረ መጥቷዋል። በጅቡቲ አድርገው ቀይ ባህርን ተሻግረው ወደ የመን የሚገቡትን ኢትዮጵያዊያንን በማገት 1000 እና 1500 የሳዑዲ አረቢያ ሪያል እና ከዛም በላይ ከወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲያስልኩ የሚያደርጉ አፋኞች መኖራችን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ መግለጼ ይታወሳል።