የኢትዮጵያውያን እና የኤርትራውያን ወጣቶች ውይይት

በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ሕዝቦች መካከል የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ሰላም እና ልማት ዓለም አቀፍ ድርጅት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ተጠየቀ። በዚሁ በአዲስ አበባ በተደረገው ውይይት ላይ የሁለቱ ሀገራት ወጣቶች ተሳታፊዎች ነበሩ።