አባይ መወያያ ይሆናል!

በቶሮንቶ ስብሰባ ጁዋር መሀመድ፣ ኦባንግ ሜቶ፣ አቶ መሐመድ ሐሰንና አበበ በላው ይናገራሉ

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሚያዝያ 29 ቀን 2003 ዓ.ም May 5, 2011)፦  ብዙ ኢትዮጵያዊያኖች ይኖሩበታል በተባለለት ቶሮንቶ ከተማ የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪው ወጣት ጁዋር መሐመድ፣ የሰብአዊ መብት ተከራካሪው ኦባንግ ሜቶ፣ አቶ መሀመድ ሀሰንና የአዲስ ድምጽ ራዲዮ አስተናጋጅ አበበ በለው የሚገኙበት ህዝባዊ ስብሰባ መሰናዳቱንና የአባይ ግድብን በሚመለከት ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ አዘጋጆቹ በተለይ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጹ።