የዓለማየሁ ሩባያት፤ ሃይኩ፤ እና ግራፊቲ

«ሩባያት፤» እና «ሃይኩ፤» የተባሉትን የሥነ ግጥም ዘይቤዎች የተከተሉትን መፅሃፎቹን ጨምሮ «ግራፊቲ፤» በሚል ርዕስ ካሳተማት ሌላ መፅሃፍ ጋር ሦሥት የግጥም መድብሎች ለንባብ አብቅቷል።

ዓለማየሁ ታዬ ይባላል። ለበርካታ ዓመታት በራዲዮና በህትመት ጋዜጠኝነትም ሠርቷል።

በግጥም ሥራዎቹ፥ በህይወትና ስነ ፅሁፍ ዙሪያ ከአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ባህልና ማኅበረሰብ ፕሮግራም ጋር የተወያየው ዓለማየሁ፤ የኦማር ኻያም ሩባያትና፥ እንዲሁም ሃይኩ የተባለው በተፈጥሮ ላይ የሚያጠነጥነው የግጥም አፃፃፍ ዘይቤ በኢትዮጵያም ብዙ ይለመዳል የሚል ዕምነት እንዳለው ይናገራል።

ያዳምጡ