የኬንያ ባለስልጣናትና ICC

የአዲሱ የኬንያ ፕሬዝደንት ዑሁሩ ኬንያታ ጠበቆች ዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ችሎት በኬንያታ ላይ የመሠረተዉን ክስ እንዲያነሳ ሰሞኑን ጠይቀዋል። ጠበቆቹ ይህን ያቀረቡት ባለፈዉ ሳምንት የፍርድ ቤቱ ጠበቆች በተመሳሳይ የተከሰሱትን የፍራንሲስ ሙታዉራን ክስ ሙሉ በሙሉ ዉድቅ ካደረጉ በኋላ ነዉ።