ኢትዮጵያዊ መልኮች በአሜሪካ – መልክአ ኢትዮጵያ ፩
ጽዮን ግርማ
የሚሳሳሙት ደንበኞቻቸው ወንድ እና ሴት ብቻ አይደሉም። አንዳንዴ ወንድና ወንድ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሴትና ሴት ሊሆኑ ይችላሉ። በዲሲ፣ በሳንፍራንሲስኮ፣ በቺካጐ እና በአትላንታ ጉብኝቴ ወንድ ለወንድ እና ሴት ለሴት ሲሳሳሙ በዐይኔ ተመልክቻለሁ። ድርጊቱን ማየት እንደመስማት እና ማውራቱ ቀላል አይደለም። ለእንደኔ ዓይነቷ ሊብራል ነኝ ባይ እንኳን መሣቀቁ ነፍስን ከሥጋ ያላቅቃል። ግን ደግሞ ያየሁትን ጽፌ ለማስነበብ ጓጉቼ ስለምጓዝ እየተሳቀቅኹም ቢሆን እንዲህ ያሉትን ቦታዎች ጐብኝቻለሁ። …