የፍርሃትና ስም ማጥፋት ፖለቲካ በኢትዮጵያ
ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሃገሬ)
2011፡ የሙስና አገዛዝ፤ ፍርሃትና ስም ማጥፋት
በዲሴምበር 2011 “ኢትዮጵያ የደም ሃገር ወይም የንቅዘት (ሙስና) ሃገር” በሚል ርእስ የኢትዮጵያን ሁለት ገጽታ በማመዛዘን አንድ ጦማር አስነብቤ ነበር። በዚያን ወቅት ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በተባለው ተቋም ተቀምጦ የነበረው ገጽታ ያሳየው ኢትዮጵያ ለም መሬቶች በተንኮል በተጠቀለለ ስውር ደባ እየተቸበቸቡ እንደነበር ነው።