አፍቃሪ ብርቱካኖችና ተናዳፊ ንቦች (ሙሉነህ ዮሐንስ)
ሙሉነህ ዮሐንስ (ከሲያትል)
ለስምንት ወራት ሙሉ በዝናብ ሲንዠቀዠቅ የነበረው የሲያትል ሰማይ ዳመናውን እየገለጠ በጉጉት ለምትጠበቀው አጭር የበጋ ፀሐይ የተመቻቸ ይመስላል። እኔም ጨቅላዋ ልጄን ከውድ ባለቤቴ ጋር ሆኜ ፀሐይ ለማሞቅ ባለኝ ጉጉት ጀንበር ሳትጠልቅ ወደቤቴ ለመድረስ የመኪና ወፈ ሰማይ ከወረረው የኢንተር ስቴት 5 ሀገር አቋራጭ አውራ ጎዳና ውስጥ እንደተዋጥኩ የእጅ ስልኬ አቃጨለች።