የወጣቷ ማህሌት XO ምግብ ቤት በመቐለ

የ21 ዓመቷ ማህሌት ሃብተማርያም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ ዓመት የሲቪል ምህንድስና ተማሪት ናት፡፡ ማህሌት መቐለ በሚገኘው ፖሊ የቴክኖሎጂ ተቋም የስነ ህንጻ ትምህርትም ትማራለች፡፡ ሁለተኛ ዓመቷ ነው፡፡

ማህሌት ጊዜዋ በትምህርት ብቻ ማዋልን ኣልመረጠችም፡፡ መቐለ ከተማ ውስጥ በኣክሱም ሆቴል ኣጠገብ የሚገኘው XO (Hug and Kiss) ምግብ ቤት ባለቤትና ስራ ኣስከያጅም ናት፡፡ ወጣቶችና የመንግስት ሰራተኞች እንግዶችና የውጭ ዜጎች በዚሁ ምግብ ቤት በሚዘጋጀው በርገርና ፒሳ ሲዝናኑ ያመሻሉ፡፡

ቤቱ ግድግዳ ውስጥ የተሰቀሉት የእህቷ የስእል ውጤቶች የተመጋቢውን የምግብ ኣምሮትን ይጨምራሉ፡፡ በጣም ለየት ባለ ቅርጽ የተገጣጠመው ወንበርና ጠረቤዛ የማህሌት የፈጠራ ውጤት ነው፡፡
ትምህርትና ስራ ባንድ ላይ ኣጣምሮ ማስኬድ ቀላል ኣይደለም ቢሆንም ግን ፍላጎት ካለ ስራና ትምህርት …