በመቀሌ ከተማ ከ5000 በላይ የሆኑ ሰላማዊ ሰልፈኞች በፌደራል ፖሊስ ተበተኑ

እነዚህ ሰልፈኞች ሰልፍ ለመውጣት የተገደዱበት ምክንያት ለአራት ዓመታት ያህል የኖርባቸው ቤቶች አስተዳደሩ እስከ ሚያዚያ 17/2003 ዓ/ም ድረስ እንዲያፈርሱ ካልሆነ ቤቶቹ በመንግስት ዶዘር እንደሚፈርሱ የሚገልፅ ደብዳቤ በየቤቱ በመለጠፉ ነው፡፡

ሰላማዊ ሰልፈኞቹ የሚኖሩባቸው ወደ ሶስት የሚሆኑ መንደሮች የራሳቸው ቤተክርስቲያን ሁሉ ያላቸው ሲሆን በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ባንዴራ፤ ታቦትና መስቀል የያዙ ቄሳውስት ተሳታፊ ነበሩ፡፡

ሰልፈኞቹ ዛሬ ሚያዚያ 13/2003 ዓ/ም በመቀሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ ደቡብ ቀበሌ “ማይ አንበሳ” እየተባለ ከሚጠራው አከባቢ ከጧቱ አስራ ሁለት ሰዓት የጀመረው ሰላማዊ ሰልፉ በመጀመሪያ ወደ አከባቢው ንዑስ ወረዳ ወይም ቀበሌ ያመራ ሲሆን ከአስተዳደሩ አጥጋቢ መልስ ሊያገኙ ባለቻላቸው ሰልፎኞቹ ወደ መቀሌ የክልሉ ፅሕፈት ቤት ለማምራት ተገዷል፡፡ ነገር ግን በጉዞ ላይ ሳሉ ከቀኑ 9:30 ብረት በታጠቁ ፌደራል ፖሊሶች ከተከበቡ በኋላ “ከዚህ ማለፍ አትችሉም ወደ መሀል ከተማም አትገቡም እርምጃ እንወስድባቸዋለን” በማለት ካስራሩዋቸው በኋላ ወደየቤታችሁ ሂዱ በማለት ኃይል እንዲበተኑ አድርጓል፡፡

ሰልፉን በካሜራ ሲቀርፅ የነበረው የጥሕሎ መፅሔት አዘጋጅ ወጣት ጋዜጠኛ ዮናስ በላይ እና ሌላ በግል በራሱ ተነሳሽነት በቪድዮ ካሜራ ሲቀርፅ የነበረ ወጣት በፌደራል ፖሊስ ተይዘው ተወስዷል፡፡ እነዚህ ወጣቶች የት እንዳሉ አይታወቅም፡፡

ሰልፈኞቹ አስተዳደሩ ቤቶቹ ስሰሩ ለዓመታት ያህል ምንም ሳይ ቆይቶ ዛሬ አፍርሱ ማለቱ አግባብ ያለመሆኑን ጠቅሰው አሁንም መልስ የማያገኙ ሌላ ሰልፍ ለማድረግ ሀሳብ አላቸው፡፡ በአሁኑ ሰዓት አንድ ቤት ለመስራት ያለው መከራ ከባድ መሆኑን ያወሱት እነዚህ ሰልፈኞች “ከቤታችን መፍረስ በፊት እኛን መግደል አለባቸው እንጂ እኛ በህይወት እያለን ቤታችንን አይፈርስም፡፡” ብለዋል፡፡

በመቀሌ ከተማ ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ውድነት በመስፋፈቱ፤ የንግድ መዛባትና የህንፃ መሳሪያዎች ስሚንቶ ጨምሮ በገዥው ፓርቲ ድርጅቶች በመኖፐል የተያዙ በመሆናቸው ህዝቡ በቀላሉ ሊያገኛቸው ባለመቻሉ ከፍተኛ የሆነ ምሬትና ቁጣ እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡