የአቦይ ስብሐት ነጋ “ይሰቀሉ፣ ሞት ይገባቸዋል!” የሚል የበቀል መንፈስ ከወዴየት ነው!?
ፍቅር ለይኩን
አቦይ ስብሐት ባለፈው ሳምንት “ከላይፍ” ወርኻዊ መጽሔት ጋር ያደረጉትን ሰላም ሰላም የማይሸት፣ ፍቅርን የተራቆተ፣ የይቅር ባይነት መንፈስ ፈፅሞ የተለየው፣ በቀልንና ጥላቻን የሚሰብክና “ዕርቅ ለመፈጸም በማለት ሰዎችን ሲልኩ የነበሩ ቄሶች ስቅላት፣ ሞት ይገባቸዋል!” የሚል የሞት ፍርድ አዋጅን የሚያስተጋባ የሚመስል ቃለ-መጠይቃቸውን እያዘንኩም፣ እያፈረኩም ለማንበብ ተገድጄያለሁ።