በስዊድን 136 000 ክሮነር ለኢሳት ተሰበሰበ
የገንዘቡ መጠን በስዊድን ከክብረወሰን ተመዝግቧል
ሙስሊሙና ክርስቲያኑ አንድነቱን ከመቼውም ጊዜ በላይ አሳይቷል
Ethiopia Zare (ሰኞ የካቲት 4 ቀን 2005 ዓ.ም. February 11, 2013)፦ ቅዳሜ የካቲት 2 ቀን 2005 ዓ.ም. በስዊድን ዋና ከተማ በስቶክሆልም በተካሄደው የኢሳት (የኢትዮጵያ ሳተላይ ቴሌቭዥን) የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት 136 ሺህ የስዊድን ክሮነር የተሰበሰበ ሲሆን፤ በዚህ ዝግጅት ላይ ሙስሊም ኢትዮጵያውን ከመቼውም ጊዜ በላይ ተሳትፎ ያደረጉበት መሆኑ ታውቋል።