የማለዳ ወግ … የ"ጅሃዳዊ ሐረካት" ዘጋቢ ፊልም መዘዝ!

ጅሃዳዊ ሐረካት Jihadawi Harekat ለማየት የጓጓነው ዘጋቢ ፊልም

ነቢዩ ሲራክ – ከሳውዲ አረቢያ

“ጅሃዳዊ ሐረካት” ዘጋቢ ፊልም ”በኢትዮጵያ እስላማዊ መንግስት ለመመስረት ከሃሳብ ያለፈ እቅድ አላቸው” የተባሉት ተጠርጣሪ አሸባሪዎችን ገመና አንጠርጥሮ ሊያሳየን መሆኑን ሞቀ ደመቅ ደመቅመቅ ያለው የኢቲቪ ማስታወቂያ ልባችን አንጠልጥሎት ከርሟል።