የመለስ፣ የጳውሎስና የቀ.ኃ.ሥ ፋውንዴሽኖች

የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ እና ፓርላማውሰሎሞን ተሰማ ጂ.

አዲስ ዘመን ጋዜጣ በጥር 9 ቀን 2005 ዓ.ም በፊት-ለፊት ገጹ ላይ የአንድን “አዋጅ መጽደቅ” ዜና አትሞ ነበር። ዜናው አዲስ አይደለም። “የአዋጁን በጆሮ” እንደሚባለው አይነት ነው። ከሁለት ቀናት በኋላ የወጣውም የአማርኛው ሪፖርተር ጋዜጣ ያንኑ ዜና ደግሞታል። ዜናውን ያነበበና የሰማ ሁሉ ወደአእምሮው የሚመጡበት ግዙፍ ጥያቄዎች አሉ። የእነዚህም ጥያቄዎች መሠረታቸው “ከፓርላማው ግልጽነት የጎደለው አሠራር” ጋር የተያያዙ ናቸው።