ታደሰ በዛብህ የመርካቶው አይጥ (ክፍል ሁለት)
በልጅግ ዓሊ
ክፍል ሁለት
“የተረፉት በሞቱት ይቀናሉ …”
“Die Űberlebenden wereden die Toten beneiden …”
ጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ የሚገኘውን የመቃብር ቦታ ግቢ ውስጥ የሚገኝ አዳራሽ አለ። ዜጎቻችንን ከዚህ ዓለም በሞት በሚለዩበት ወቅት አስከሬኑን ወደ ሃገራችን መላክ የተለመደ ቢሆንም፣ አንዳንዴ እንደ ሟች ወይም እንደ ሟች ቤተሰብ ፍላጎት የቀብሩ ሥነ ስርዓት እዚሁ ፍራንክፈርት ውስጥ ይፈጸማል።