ወያኔ መቼ ይሆን እራሱን የሚያየው?

ይኸነው አንተሁነኝ

የታየው ድንገት የሚጠፋበት፣ የተፈለገው ለመድኃኒት ያክል እንኳ የሚታጣበት፣ ከኔ ጋር ነው ተብሎ የነበረው ሳይታሰብ የሚለይበትና ስምምነት የተደረሰበት ሳይቆይ የሚፈርስበት ወቅት። ሰዓታት ወቅቶችና ዓመታት ብቻ አይደሉም ትእይንቶችም እንደ ሸማኔ መወርወሪያ እየተምዘገዘጉ ነው። ጎን ለጎን ከአቻ የስልጣንና የደረጃ ጓደኛ ጋር፤ ከላይ ወደ ታች ወይም ከታች ወደ ላይ አለቃ ከምንዝር ምንዝር ካለቃ ሳይለይ የሚቧደኑበት የሚተሻሹበት የሚጓተቱበት ዘመን። ዘመነ ጭንቅ ንትርክ።