የመለስ ራዕይ በ”አዲስ ታይምስ” መጽሔት ተተገበረ!!!

ተመስገን ደሳለኝ / Temesgen Dessalegneተመስገን ደሳለኝ

ምንም ጥርጥር የለውም መለስ ዜናዊ ፍፁም አምባገነን ነበር። ምንም ጥርጥር የለውም ከአንድ ክፍለ ጦር በላይ የተለየ ሀሳብን እና ነፃ ሚዲያን ይፈራል። ምንም ጥርጥር የለውም ወራሾቹም ሀሳቡን በነፃነት የሚገልፅን ከመለስ በባሰ መልኩ ይፈራሉ። ይህ ፍራቻቸው ወደ ጭፍን አምባገነንነት ስለቀየራቸው መላ ሀገሪቷን ወደ ድቅድቅ ጨለማ እየገፏት ነው።