የሌለ ዲሞክራሲ ይሰጣልን?
ይኸነው አንተሁነኝ
ከታላቋ ሩሲያ መከፋፈልና ከኮሚኒዝም ርዕዮተ ዓለም መንኮታኮት በኋላ ጥቂት የማይባሉ ሀገሮች እና ለለውጥ እንታገላለን ሲሉ የነበሩ ድርጅቶች መመሪያችን ነው እያሉ ሲያመልኩት የኖሩትን የሶሻሊዝም አይዲዮሎጂ፤ የተናገሩት ሳያቅራቸው የጻፉት ሳያሳፍራቸው ባንዲት ጀንበር እርግፍ አድርገው፤ ጥቅም እስከተገኘ ድረስ በሉ የተባሉትን ለማለት ሁኑ የተባሉትን ለመሆን ተሯሯጡ። እጃችሁ ከምን እያሉ ሲያባብሏቸው የነበሩትን የትላንት ወዳጅ መከታ ሀገሮችን ረሱ።