አማናዊ ‘ሕዳሴ’ ይሉሃል ይኼ ነው!!

ኤፍሬም እሸቴ

ከዚህ በፊት አንዲት ተውሼ ለራሴ ያሻሻልኳትን ግጥም ነግሬያችሁ ነበር። የግጥሟ ባለቤት የአብዬ መንግሥቱ ለማ አባት የኔታ ለማ ኃይሉ ወልደ ታሪክ ናቸው። መጽሐፋቸው በድጋሚ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስለታተመ ምራቁን የዋጠ፣ ታሪክ የሚወድ፣ ማንነቱን የሚፈልግ ማንም ኢትዮጵያዊ ሊያነበው የሚገባ “ባዮግራፊ” ነው። አገር ቤት የሚሄድ የአሜሪካ ነዋሪ ባገኘኹ ቁጥር “ይኼንን መጽሐፍ ሳትገዛ/ዢ እንዳትመጣ/ጪ” እላለኹ። አንዴ ያነበበው መድገሙ እንደማይቀር እርግጠኛ ነኝ።