ከቢፒ.አር. በኋላ የመንግስት ተቋማት አገልግሎቶች ብቃት እና ጥራት ቀንሷል ተባለ

የአዲስ አበባ ዘጋቢ ሰሞኑን በላከልን ዜና ወያኔ ሊቃወሙኝ ይችላሉ ብሎ የሚሰጋቸውን ሰዎች ከመንግሥት መሥሪያቤቶች ለመመንጠር የተጠቀመበት የቢፒአር ፖሊሲ ቀደም ሲል አገልግሎታቸው ደካማ የነበሩትን መንግሥታዊ ተቋማትን ይበልጥ እየገደለ መሆኑንን ለተቋሞቹ ቅርበት ያላቸው በርካታ ሰዎች ቅረታ እያሰሙ መሆናቸው ታውቆአል።

የወያኔ የአገዛዝ ሥር ዓቱን በመላው አገሪቱ ለማስፈንና ጸረ አገሪ ዕቅዱን ለማስፈጸም በቂ የሥልጣን እድሜ ለማግኛ የተጠቀመበት ቢ.ፒ.አር. ወይም “ቢዝነስ ፕሮሰሲንግ ሪቪው”ስለአገራቸውና ህዝባቸው በሚጨነቁ ሌሎች አገራት ደካማ አሰራርን ለማስወገድን በምትኩ ምርታማና ቀልጣፋ የሆነ አሰራር በሥራ ላይ ለማዋል ረድቶአል። ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ ግን በሰራተኞች ብቃት እና ትምህርት ፈንታ የፖለቲካ አመለካከቶቻቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት አይደግፉኝም ብሎ የገመታቸውን በማባረር ተቋማቱን በካድሬዎቹ እና በግዳጅ የፓርቲ አባላት ማስወረሩ ይታወቃል።

ዘጋቢያችንን ተዘዋውሮ ያናገራቸው አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፥ በተለይም ወደ መንግስት ሆስፒታሎች መሄድ በሽታ የሚጨምር ሆኗል ብለዋል። እርጉዝ ሴቶችን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ሆስፒታሎች እና ጤና ጥበቃ ተጠቃሚዎች ስላሽቆለቆለው የአገልግሎት ደረጃ አማረው፤ ይህም ልምድ ያላቸው የቀድሞ ሰራተኞች መባረራቸውን ተከትሎ ከተከሰተ መመሰቃቀል ጋር የተያያዘ ነው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።