ልማታዊው ኪስ አውላቂ

ክንፉ አሰፋ

የ‘ህዳሴው ቦንድ’ ግዢ ግርግር ሞቅ ብሎ በነበረበት ሰሞን ይነገር የነበረ አንድ ቀልድ አለ። የ‘ማረሚያ’ ቤት ፖሊሶች እና ታጋዮች 500 ብር በሰረቀ ሌባ ላይ ውይይት ያደርጋሉ። ተከሳሹ ብሩን ያላግባብ ይስረቅ እንጂ በገንዘቡ የህዳሴውን ቦንድ መግዛቱ ነው ጉዳዩን ለውይይት የዳረገው። ይህ ሌባ መታሰር የለበትም የሚሉት ታጋዮች፣ ለፖሊሶቹ ያቀረቡት መከራከሪያ ነጥብ “ልማታዊ ሃሳብ” ነበር።