ማፈራረስ ማተራመስ ማሸበር- የወያኔ ታላቁ ራዕይ

ይኸነው አንተሁነኝ

“መካብ ሲያቅት ማፍረስ ሥራ ይሆናል”ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

ወያኔ ላለፉት 21 ዓመታት የሀገራችንን ታሪክ ለማፈራረስና ለመቀየር የቻለውን ሁሉ ሞክሯል። የሕዝባችንን የአልደፈርም ባይነት ወኔ ለመስለብና ለማኮላሸት ያልቆፈረው ጉድጋድ አልነበረም። ሃይማኖታዊ ስርአታችንንና ወጋችንን ለመናድ ብዙ መንገድ በመጓዝ ደክሟል። አብሮ በመቻቻል የመኖር ወጥ ባህላችንን ለመጨፈላለቅና ለማጥፋት ሞክሯል።