የሰሞኑ ጦማሮች እፍታ
በማሕሌት ፋንታሁን
በኢትዮጵያ የሚገኙ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ቁጥር በባለፈው ዓመት 246,360 የነበረው በአሁኑ ዓመት በአስገራሚ ፍጥነት 839,580 መድረሱንና ነገር ግን ካለን የሕዝብ ብዛት ሲነፃፀር 0.95 ፐርሰንት ያክሉ ብቻ ተጠቃሚ እንደሆነና ከዚህም ውስጥ የገዢው ፓርቲ ቤተሰቦችና ደጋፊዎች እንደሚበዙ – ከሌሎች ሃገራት ጋር በማነፃፀር ያስነበበን ኢትዬ ቼንጅ የተሰኘ ጦማር ነው፡፡ ሙሉው እዚህላይ ይገኛል፡፡
አብዪአዲ የሚገኘውና በጀግናውራስ አሉላ አባነጋ ስም ተሰይሞየቆየው የሁለተኛ ደረጃት/ቤት ስያሜው ተቀይሮ በመለስዜናዊ ስም እንዲሰየም መወሰኑን ታማኝምንጮች ማስታወቃቸውን የገለፀው ይኸው ኢትዮ ቼንጅ ጦማር ሲሆን የተጻፈው በኢየሩሳሌም ስዩም ነው፡፡ “በደርግዘመን የተሰራውና በራስ አሉላስም ተሰይሞ የ 9-10ኛክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምርከቆየ በኋላ ከ2002 ዓ.ምጀምሮ የት/ቤቱን አቅም ለማሳደግ በሚል የ11-12ኛመማሪያ ክፍሎችን ለመገንባትበአገር ውስጥና በውጭአገራት የሚገኙ የአካባቢውተወላጆች ገንዘብ አዋጥተውሥራው መከናወኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል።ግንባታው ተጠናቆ ባለፈውነሐሴ ወር ለማስመረቅ በዝግጅት ላይእንዳለ አቶ መለስበማለፋቸው ፕሮግራሙ መሰረዙንሲታወቅ፣ ከሁለት ሳምንትበፊት በተከናወነው የምረቃ ሥነ–ስርአትየክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናትበስፍራው እንደተገኙ ማወቅተችሎዋል።” ሙሉው እዚህ ላይ ይገኛል፡፡
ይሄው ጦማር ባሳለፍነው እሁድ ኅዳር 16/2005ዓ.ምን አንድነት ፓርቲ አዘጋጅቶት በነበረው ፕሮግራም ላይ የውይይቱ አቅራቢ እና የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ‹የወቅቱየአገራችን የፖለቲካ ሁኔታናየወደፊት የትግል አቅጣጫ› በሚል አርዕስት ያቀረቡትን ጽሑፍም አስነብቦናል፡፡ ሙሉው እዚህ ላይ ታገኙታላችሁ፡፡
ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ ሁለት የሃገራችን ከፍተኛ የጦር አመራሮች፤ የመከላከያ ሚኒስቴሩ አቶ ሲራጅ ፋጌሳ እና ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ኢንቨስትመንትን ለማስተዋወቅ በሚል ምክንያት መሄዳቸውን በተመለከተ መግለጫ ሳይሰጥ ዋሽንግተን ዲሲ እንደሚገኙ የሚያወራው ኢትዮ ሴንተር ጦማር ነው፡፡ ሙሉው እዚህላይ ይገኛል፡፡
“ለሕሊና እስረኞች የሚሟገተው ፍሪደም ናው (‘Freedom Now’) የሚባለው ድርጅት የእስክንድር ነጋን ጉዳይ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያላግባብ የታሠሩ ሰዎችን ጉዳይ ለሚያጠናው ግብረኃይል ማቅረቡ ታወቀ።” የሚለን ፊንፊኔ የተሰኘ ጦማር ነው፡፡ በተጨማሪም ግብረ ኃይሉ በቀረበለት መመልከቻ ላይ በመጭው ሚያዝያ ውሣኔ እንደሚሰጥ እንደሚጠበቅም ገልጧል።
“የመጨረሻዎቹ ቤተ እስራኤላውያን ወደ እስራኤል ለመጓዝ ተዘጋጅተዋል::130,000 ኢትዮጵያውያን ይሁዲዎች ወደ እስራኤል ይበራሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው:: በማርች2014 ይጠናቀቃል ተብሎ የታቀደው ይህ ኦፕሬሽን የኢትዮጵያ የጥንት ታሪክ ምዕራፍ መዝጊያ ተደርጎ ታስቧል::” የሚለን ደግሞ የሚኒሊክ ሳልሳዊ ጦማር ነው፡፡ AFPን ጠቅሶ ያቀረበውን ሙሉ መረጃ እዚህላይ ያገኙታል፡፡
እዚህ የዞን ዘጠኝ ጦማር ላይ ደግሞ በፍቃዱ ኃይሉ የመቀሌ የአንድ ቀን ቆይታውን ‹የጉዞ ማስታወሻ፤ መቐለን በአንድ ቀን› በሚል ርዕስ ያስነበበን ሲሆን ስለ መቐሌ ከተማዋና ሕዝቦቿ፣ የአፄ ዮሓንስ ቤተ መንግሥት፣ የሰማዕታት መታሰቢያ እና ሙዚየም በአንድ ቀን እንደታዘበው ያቀረረበበት ነው፡፡ ሙሉውን እዚህ ላይ ታገኙታላችሁ፡፡