የዛሬ አበባዎች

ኤፍሬም እሸቴ

ልጅነት የንጽሕና እና የንፁህ ልብ ዕድሜ ዘመን እንደሆነ በሁሉም ሰው፣ በሁሉም ባህልና እምነት ይታመናል። ይህ እውነት መሆኑን ወላጅ የሆነ ሰው ወይም ለሕጻናት ቅርበት ያለው ሰው ጥናትም ባያደርግ ይረዳዋል። ሁላችንም በልጅነት ዕድሜ ስላለፍን በርግጥም እኛም ምስክሮች ነን።