ተው ስማኝ ሀገሬ …

አቡ ዘኪያ ከምድረ-አናቶሊያ

ኢሕአዴግ በሀገራችን ዴሞክራሲ ማስፈኑንና ሕገ-መንግሥታዊ ስርዓት መዘርጋቱን ሌት ተቀን ይተርክልናል። እውነታው ግን ሀገራችን በ81 ዓመት የሕገ-መንግሥት ታሪኳ ውስጥ አንድም ጊዜ እደግመዋለሁ አንድም ጊዜ ሕገ- መንግሥታዊ ስርዓት ለማየት አልመታደሏ ነው። የኢሕአዴግ አብዮታዊ ዴሞክራሲ ፀረ-ዴሞክራሲ አብዮት ነው። ኢሕአዴግ ሕገ-መንግሥቱን የወረቀት ላይ ነብር አድርጎታል። ተቃዋሚዎችን በፀረ-ሕገ መንግሥታዊነት የሚነቅፈው ኢሕአዴግ የሕገ-መንግሥቱ ቀንደኛ ባላንጣ ነው …