ሰብአዊ መብትና መንግሥታዊ ግፊት በኢትዮጵያ (2012)

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም / ትርጉም ነጻነት ለሃገሬ

በዲሴምበር 2008 ላይ በኢትዮጵያ የ”ለውጥ የሌሽ ዓመት” በማለት እንጉርጉሮ መሰል መልእክት ጽፌ ነበር።

2008 የ2007፤ 2006፤ 2005፤ 2004 ቅጂ ነበር … በየቀኑ ኢትዮጵያዊያን ሲነቁ ልክ እንደተሰበረ የሙዚቃ ሸክላ ባለፈው የሕይወት ስቃያቸው ድግግሞሽ መከራ ውስጥ በመዳከር ነበር የሚገኙት። እያንዳንዱ አዲስ ቀን ካለፈው የወረሰውን ይዞ ነበር የሚመጣው።