መጪው ምርጫና የአካባቢ ሥልጣን ጥያቄ

በየማነ ናግሽ

ኢትዮጵያ በመጪው ሚያዝያ ወር የአካባቢና የአዲስ አበባ መስተዳደር ምርጫ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ነች፡፡ ባለፉት አራት የአካባቢ ምርጫዎች ዋነኛ ተቃዋሚዎች ራሳቸውን ከምርጫ ማግለላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት በሒደቱ ለመሳተፍ ፍላጎት አጥተው ነው በሚል መንግሥት ይተቻቸዋል፡፡