“ስወድሽ” – ሚካኤል በላይነህና ገብረ ክርስቶስ ደስታ

ምርጥ ሥዕሎቹና የግጥም ሥራዎቹ ዘመን ተሻግረው ዛሬም የአያሌ ሚልዮን ኢትዮጵያውያን የኪነ-ጥበብ አድናቂዎችን ቀልብ እንደሳቡ ነው፤ ሠዓሊና ገጣሚ ገብረክርስቶስ ደስታ።

የጥበብ አዋቂዎች በታላቅ አድናቆትና አክብሮት የሚያወሱት ይህ ሠው በህይወት ካለፈ ሦሥት አሥርታት ቢቆጠሩም፥ “ስወድሽ-ስወድሽ’ን” የመሳሰሉ ውብ ህያው ሥራዎቹ አዲስ ነፍስ ዘርተውና ገዝፈው በሌላ ግሩም ሥልት ተቀምመው በጆሯችን መንቆርቆር ከበቁት ምናልባትም ቀዳሚ እንጂ የመጨረሻ ከማይሆኑ ሥራዎቹ ውስጥ ናቸው።

ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ በቅርቡ «ናፍቆት፤» በሚል ርዕስ ከአድማጭ ጆሮ ያደረሰው አዲስ ሲዲው ከተካተተችው “ስወድሽ” ዙሪያ እናወጋለን።

ከሚካኤል በላይነህ ጋር ያደረግነውን ወግ ከዚህ ያድምጡ።